አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

አባታችን የተሳሳተውን ንጉሡን ይገሥጻል

ኢዩ የሚመለሰውን ንጉሥ በጥያቄ ይቀበለዋል፦ ኃጢአተኛውን ልትረዳ ይገባሃልን? ኢዮሣፍጥ ሕዝቡን በመዞርና ፈራጆችን በመሾም ይመልሳል፤ ለሰው ሳይሆን ለአብ እንደሚፈርዱ፣ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ፣ አድልዎ ወይም መማለጃ እንደሌለ ይነግራቸዋል።

ምዕራፍ 19።

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤቱ በሰላም ተመለሰ። ባለ ራእዩ የሐናኒ ልጅ ዩሁ ንጉሡን ኢዮሣፍጥን አግኝቶ እንዲህ አለው፤ “ክፉዎችን ትረዳና አባታችንን የሚጠሉትን ትወዳለህን? ስለዚህ ከአባታችን ዘንድ ቍጣ በአንተ ላይ መጥቶአል። ሆኖም መልካም ነገር በአንተ ተገኝቶአል፤ የአሼራ ዐፀዶችን ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ አባታችንንም ለመሻት ልብህን አዘጋጅተሃል።”

ኢዮሣፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ እንደ ገናም ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ኤፍሬም ተራራማ አገር ድረስ በሕዝቡ መካከል ወጣ፤ ወደ አባታችን ወደ አባቶቻቸው አምላክም መለሳቸው። በምድሪቱ ውስጥ በይሁዳ በተመሸጉ ከተሞች ሁሉ ከተማ በከተማ ዳኞችን ሾመ። ዳኞቹንም እንዲህ አላቸው፤ “የምታደርጉትን ተመልከቱ፤ ለሰው ሳይሆን ለአባታችን ትፈርዳላችሁና፤ በምትፈርዱበትም ጕዳይ ሁሉ እርሱ ከእናንተ ጋራ ነው። አሁንም የአባታችን ፍርሃት በእናንተ ላይ ይሁን፤ ተጠንቅቃችሁ አድርጉ፤ በአባታችን ዘንድ ዐመፅም ሆነ አድልዎ ወይም ጕቦ የለምና።”

ኢዮሣፍጥ ደግሞ የአባታችንን ፍርድ ይፈጽሙ ዘንድና ክርክሮችን ይፈቱ ዘንድ ከሌዋውያን፣ ከካህናትና ከእስራኤል የአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶችን በኢየሩሳሌም ሾመ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ። አዘዛቸውም፤ “አባታችንን በመፍራት፣ በታማኝነትና በፍጹም ልባችሁ እንዲህ አድርጉ። በከተሞቻቸው የሚኖሩ ወንድሞቻችሁ ስለ ደም ማፍሰስ ወይም ስለ ሕግና ትእዛዝ፣ ስለ ሥርዐትና ፍርድ ክርክር ባመጡላችሁ ጊዜ ሁሉ፣ በአባታችን ፊት በደለኞች ሆነው በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ ቍጣ እንዳያመጡ አስጠንቅቋቸው፤ እንዲህ ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም። አሁንም ሊቀ ካህናቱ አማርያ በአባታችን ነገር ሁሉ ላያችሁ ነው፤ የእስማኤል ልጅ ዘባድያም የይሁዳ ነገድ አለቃ በንጉሡ ነገር ሁሉ ላያችሁ ነው። ሌዋውያኑም በፊታችሁ ሹማምት ሆነው ያገለግላሉ። በርቱ፤ አድርጉም፤ አባታችንም መልካም ከሚያደርጉት ጋራ ይሁን።”