አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

አጽናናኸኝ

ከፍርድ በኋላ ላለው ቀን አጭር መዝሙር። ዘማሪው ስለ ተመለሰው ቁጣና ስለ መጣው መጽናናት አብን በግልጽ ያመሰግናል፤ እታመናለሁ አልፈራምም ይላል። ውሃ በደስታ ይቀዳል፤ ቅዱሱ ቅርብ ስለሆነ ጽዮን ትዘምራለች።

ምዕራፍ 12።

በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “አባቴ ሆይ፣ አመሰግንሃለሁ፤ በእኔ ላይ ተቈጥተህ የነበርህ ብትሆንም፣ ቍጣህ ተመልሷል፤ አንተም አጽናናኸኝ።” እነሆ፣ አባታችን መዳኔ ነው፤ እታመናለሁ፤ አልፈራም፤ አባቴ ኀይሌና መዝሙሬ ነውና፤ እርሱም መዳኔ ሆኗል። ከመዳን ጕድጓዶች በደስታ ውሃ ትቀዳላችሁ። በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “አባታችንን አመስግኑ፤ ስሙን ጥሩ፤ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ፤ ስሙ ከፍ ከፍ እንዳለ አውጁ። ለአባታችን ዘምሩ፤ ድንቅ ነገር አድርጓልና፤ ይህም በምድር ሁሉ ይታወቅ። አንቺ የጽዮን ነዋሪ ሆይ፣ ጮኸሽ እልል በዪ፤ በደስታም ዘምሪ፤ የእስራኤል ቅዱስ የሆነው አባታችን በመካከልሽ ታላቅ ነውና።”