አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

ክፉ ገዦች

ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ዜማ የተዘመረ፤ የዳዊት መዝሙር፤ ወርቃማ መዝሙር።

ከፍርድ ወንበር ዓመፅን በሚያድሉ ዳኞች ላይ የቀረበ ክስ። መርዘኞች ተብለው፣ የአስማተኛውን ዜማ ላለመስማት ጆሮውን እንደሚደፍን እባብ ደንቆሮዎች ተብለው ይጠራሉ። ሰዎች አብ በምድር ላይ እንደሚፈርድ በግልጽ እንዲናገሩ ጸሎቱ ክራንቻቸው እንዲሰበር ይለምናል።

ምዕራፍ 58።

እናንተ ገዦች ሆይ፤ በእርግጥ ትክክለኛውን ትፈርዳላችሁን? የሰውን ልጆች በቅንነት ትዳኛላችሁን? a a v1 “አታጥፋ” ይህ መዝሙር ይዘመርበት የነበረው የዜማ ስም ነው። አይደለም፤ በልባችሁ ዐመፅን ታውጠነጥናላችሁ፤ እጆቻችሁ በምድር ላይ ዐመፅን ያከፋፍላሉ። ክፉዎች ከማኅፀን ጀምሮ የተለዩ ናቸው፤ ከተወለዱበት ጀምሮ እየተሳሳቱ ውሸትን ይናገራሉ። መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ ጆሮውን እንደሚደፍን እንደ ደንቆሮ እፉኝት ነው፤ ይኸውም የአስማተኞችን ድምፅ፣ የብልጥ ጠንቋይንም ድምፅ እንዳይሰማ ነው። አባታችን ሆይ፤ በአፋቸው ያሉትን ጥርሶች ስበር፤ አባታችን ሆይ፤ የወጣት አንበሶችን መንጋጋ ጥርስ ንቀል! እንደሚፈስ ውሃ ይጥፉ፤ አባታችን ፍላጻዎቹን ሲያነጣጥር ይቈረጡ። ሲንቀሳቀስ እንደሚመሽ ቀንድ አውጣ፣ ፀሐይን እንደማያይ ጨንግፎ እንደተወለደ ሕፃን ይሁኑ። ማሰሮዎቻችሁ የእሾኹን ሙቀት ሳያውቁ፣ ልምሉም ቢሆኑም የነደዱም ቢሆኑ፣ እርሱ ጠራርጎ ያስወግዳቸዋል። ጻድቃን ፍርድ ሲፈጸም አይተው ደስ ይላቸዋል፤ እግሮቻቸውን በክፉዎች ደም ውስጥ ይታጠባሉ። ሰዎችም፣ “በእርግጥ ለጻድቃን ዋጋ አለ፤ በእርግጥ አባታችን ምድርን ይዳኛል” ይላሉ።