አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

አብ የኤዶምን የጥንት ጥላቻ ይፈርዳል

በሴይር ተራራ ያለው ኤዶም የጥንት ጥላቻ ይዞ በመከራ ቀን እስራኤልን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ፤ ከዚያም ባዶ የቀሩትን ሁለቱን አገሮች የራሱ አደረገ። አብ ባዶ የሚሆነው ኤዶም እንደ ሆነ፣ ለዘለቄታውም እንደ ሆነ ይመልሳል።

ምዕራፍ 35።

የአባታችን ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን በሴይር ተራራ ላይ አዙር፤ በእርሱም ላይ ትንቢት ተናገር። እንዲህ በለው፦ ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፦ “ሴይር ተራራ ሆይ፣ እነሆ፣ በአንተ ላይ ነኝ፤ እጄንም በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ምድረ በዳ አደርግሃለሁ። ከተሞችህን ፍርስራሽ አደርጋለሁ፤ አንተም ባድማ ትሆናለህ። እኔም አብ እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።

የጥንት ጥላቻ ስለ ያዝህ፣ የእስራኤልንም ሕዝብ በጥፋታቸው ጊዜ፣ የመጨረሻው ቅጣታቸው በመጣበት ጊዜ ለሰይፍ አሳልፈህ ስለ ሰጠህ፣” ስለዚህ፣ ሕያው ነኝና፣ ይላል ጌታ አባታችን፣ ለደም ማፍሰስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ ደምም ያሳድድሃል። ደም ማፍሰስን ስላልጠላህ፣ ደም ያሳድድሃል። “ሴይር ተራራን የተፈታ ባድማ አደርገዋለሁ፤ ከእርሱም የሚመጣውንና የሚሄደውን ሁሉ አጠፋለሁ። ተራራዎቹን በታረዱት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኰረብቶችህ፣ በሸለቆዎችህና በጅረቶችህ ሁሉ በሰይፍ የተገደሉት ይወድቃሉ። ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ባዶ ሆነው ይቀራሉ። እኔም አብ እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።

‘እነዚህ ሁለት ሕዝቦች፣ እነዚህ ሁለት አገሮች የእኔ ይሆናሉ፤ እንወርሳቸዋለን’ ብለህ ስለ ተናገርህ፣ አባታችን በዚያ የነበረ ቢሆንም፣” ስለዚህ፣ ሕያው ነኝና፣ ይላል ጌታ አባታችን፣ እስራኤልን በመጥላትህ ባሳየኸው ቍጣህና ቅናትህ ልክ አደርግብሃለሁ፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ መካከል ራሴን አስታውቃለሁ።

እኔም አብ እንደ ሆንሁ ታውቃለህ። በእስራኤል ተራራዎች ላይ የተናገርኸውን ስድብህን ሁሉ ሰምቻለሁ፦ “ባድማ ሆነዋል፤ እንድንበላም ተሰጥተውናል።” በአፍህ በእኔ ላይ ተመካህ፤ ቃላትህንም በእኔ ላይ አበዛህ፤ እኔም ሰማሁ። ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ደስ በሚላት ጊዜ፣ አንተን ባድማ አደርግሃለሁ። የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ ደስ እንዳለህ፣ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። አንተ ሴይር ተራራ ሆይ፣ ኤዶምም ሁሉ፣ ሁሉም ባድማ ትሆናለህ። እነርሱም እኔ አብ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።