አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

አሽዶድ በአሦር እጅ ወደቀች

አብ ኢሳይያስን ማቅና ጫማውን አውልቆ ለሦስት ዓመት ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንዲሄድ ይነግረዋል — ተጋልጠው የሚነዱ ምርኮኞች ሕያው ምስል። ይህም በእነዚያ አጋሮች ላይ ባለው የይሁዳ መታመን ላይ ያነጣጠረ ነው። የባሕሩ ዳርቻ እንዴት እናመልጣለን ብሎ ይጠይቃል።

ምዕራፍ 20።

በአሦር ንጉሥ በሳርጎን ተልኮ የጦር አዛዡ ወደ አሽዶድ በመጣበት ዓመት፣ አሽዶድን ወግቶ ያዛት።

በዚያን ጊዜ አባታችን በአሞጽ ልጅ በኢሳይያስ አማካይነት፣ “ማቅህን ከወገብህ ፍታ፤ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ” አለ። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕራቁቱንና ባዶ እግሩን እየሄደ ኖረ። ከዚያም አባታችን እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብፅና በኵሽ ላይ ምልክትና ትእምርት እንዲሆን፣ ዕራቁቱንና ባዶ እግሩን ሦስት ዓመት እንደ ሄደ ሁሉ፣ a a v3 ኵሽ አሁን ሱዳንንና የሰሜን ኢትዮጵያን የሚሸፍነው አካባቢ ጥንታዊ ስም ነው። እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብፅን ምርኮኞችና የኵሽን ግዞተኞች፣ ወጣቱንም ሽማግሌውንም ዕራቁታቸውን፣ ባዶ እግራቸውን፣ መቀመጫቸው ተገልጦ ይነዳቸዋል፤ ይኸውም የግብፅን ኀፍረት ያጋልጣል። ከዚያም ተስፋቸው በሆነችው በኵሽና ትምክሕታቸው በሆነችው በግብፅ ምክንያት ይደነግጣሉ፤ ያፍራሉም። በዚያም ቀን የዚህ ባሕር ዳርቻ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፤ ‘እነሆ፣ ከአሦር ንጉሥ እንድንድን ለርዳታ የሸሸንበት ተስፋችን እንዲህ ሆነ! እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’”