አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

የአባታችን ሰይፍ በፍልስጥኤም ላይ ይወርዳል

የአብ ጐርፍ ከሰሜን ተነሥቶ ፍልስጥኤምን አጥለቀለቀ፤ ድንገተኛነቱ ታላቅ ስለሆነ አባቶች ወደ ልጆቻቸው ዘወር አይሉም። ጋዛና አስቀሎና ያለቅሳሉ። በመጨረሻም ሰይፉ እስከ መቼ ድረስ አታርፍም ተብሎ ይጠየቃል፤ መልሱም፦ ገና ትእዛዝ እያለበት አያርፍም የሚል ነው።

ምዕራፍ 47።

ፈርዖን ጋዛን ከመምታቱ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የአባታችን ቃል ይህ ነው።

አባታችን እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፣ ውሃ ከሰሜን ይጎርፋል፣ ተጥለቅላቂ ጎርፍም ይሆናል። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ይጮኻል፣ በምድሪቱ የሚኖርም ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል። በፈረሶቹ ኮቴ ድምፅ፣ በሠረገላዎቹ ጩኸትና በመንኰራኵሮቹ ግሥጋሤ፣ አባቶች እጆቻቸው ዝለው ስለ ልጆቻቸው ወደ ኋላ አይመለሱም፣ ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት የሚመጣው ቀን ስለ ደረሰ፣ ሊረዳ የሚችለውን የተረፈውን ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ ነው። አባታችን ፍልስጥኤማውያንን፣ ከከፍቶር ባሕር ዳርቻ የቀሩትን ያጠፋልና። ጋዛ በሐዘን ራሷን ትላጫለች፤ አስቀሎና ዝም ትሰኛለች። እናንተ የሸለቆአቸው ቀሪዎች ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ሰውነታችሁን ትተለትላላችሁ? ወዮ፣ የአባታችን ሰይፍ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አታርፍም? ወደ ሰገባህ ተመለስ፤ ጸጥ በልና ዕረፍ። አባታችን ትእዛዝ ከሰጠው ታዲያ እንዴት ሊያርፍ ይችላል? በአስቀሎና ላይና በባሕሩ ዳርቻ ላይ፣ ወደዚያ መርቶታል።”