አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

ሰባት ጊዜ የነጠረ ብር

ለመዘምራን አለቃ፤ በሰመኒት እንዲዘመር፤ የዳዊት መዝሙር።

ታማኞች ጠፍተዋል፤ ሁሉም በሁለት ልብ ይሸነግላል። ዘማሪው የሚመኩ ምላሶች እንዲቈረጡ ይለምናል፤ መልስም ያገኛል፦ ችግረኞች ስለሚያቃስቱ አብ «እነሣለሁ» ይላል። ቃሎቹ ሰባት ጊዜ የነጠሩ ብር ናቸው።

ምዕራፍ 12።

አባታችን ሆይ፣ እርዳን፤ ታማኞች ጠፍተዋልና፤ ቅኖች ከሰው ልጆች መካከል ተሰውረዋል። ሰው ሁሉ ለባልንጀራው ይዋሻል፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ። አባታችን የሽንገላን ከንፈር ሁሉ፣ ታላቅ ነገርን የሚመካውን ምላስ ሁሉ ይቍረጥ፤ “በምላሳችን እናሸንፋለን፤ ከንፈሮቻችን የራሳችን ናቸው፤ በእኛ ላይ ጌታ ማን ነው?” የሚሉ ናቸው።

“ድኾች ስለ ተበዘበዙ፣ ችግረኞችም ስለሚያቃስቱ፣ አሁን እነሣለሁ” ይላል አባታችን፤ “የሚናፍቀውን ሰው ወደ ደኅንነት አወጣዋለሁ።”

የአባታችን ቃላት ንጹሕ ቃላት ናቸው፤ በእቶን ውስጥ እንደ ነጠረ ብር፣ ከምድር የሆነ፣ ሰባት ጊዜ የተጣራ። አንተ አባታችን፣ ችግረኞችን በደኅና ትጠብቃቸዋለህ፤ ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቀናለህ። በሰው ልጆች መካከል ርኵሰት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣ ኀጥኣን በየአቅጣጫው ይዞራሉ።