አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

ቅን ነገር የሚያደርግ የለም

ለመዘምራን አለቃ፤ እንደ መሃላት ዜማ የተዘመረ፤ የዳዊት የጥበብ መዝሙር።

ከመዝሙር 14 ጋር ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል። አብ የሚያስተውል አንድ ሰው ፍለጋ የሰውን ልጆች ሁሉ ይመለከታል፤ አንድም አያገኝም። ሕዝቡን የሚበሉ፣ የሚያስፈራ ነገር በሌለበት ፍርሃት ይይዛቸዋል። ከጽዮን የሚመጣውን ማዳን በመናፈቅ ይደመደማል።

ምዕራፍ 53።

ተላላው በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ጠማሞች ናቸው፤ አስጸያፊ በደልን ያደርጋሉ፤ ቅን ነገር የሚያደርግ የለም።

አስተዋይ ያለ፣ አባታችንን የሚሻ ይኖር እንደ ሆነ ያይ ዘንድ፣ አባታችን ከሰማይ በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ተመለከተ። ሁሉ ተስተዋል፤ በአንድነት ጠማማ ሆነዋል፤ ቅን ነገር የሚያደርግ የለም፤ አንድ ስንኳ የለም።

እንጀራ እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚበሉ፣ አባታችንንም የማይጠሩ፣ የክፋት አድራጊዎች እውቀት የላቸውምን? የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ በታላቅ ፍርሃት ተውጠው ነበር፤ አባታችን በአንተ ላይ ያደፈጠውን ሰው ዐጥንት በትኖአልና፤ አባታችን ጠልቶአቸዋልና አሳፈርሃቸው።

ለእስራኤል የሚሆን ድነት ከጽዮን ምነው በወጣ! አባታችን የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ያዕቆብ ደስ ይበለው፣ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።