አሁን በኅትመት ይገኛል
መጽሐፍ

ዮናስ በጥልቁ ውስጥ

ዮናስ ከዓሣው ሆድ ውስጥ እንደ ሰጠመ ሰው ይጸልያል፤ የባሕር አረም ራሱን ተጠምጥሞ የምድር መዝጊያዎች ከኋላው ተዘግተው ሳሉ፣ ሕይወቱን ከጕድጓድ ስላወጣ አብን ያመሰግናል። የተሳለውን እንደሚፈጽም ይሳላል፣ ዓሣውም በየብስ ላይ ይተፋዋል።

ምዕራፍ 2።

ከዚያም ዮናስ ከዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አባታችን እንዲህ ሲል ጸለየ፤ በመከራዬ ጊዜ አባቴን ጠራሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከመቃብር ሆድ ውስጥ ሆኜ እርዳታ ለማግኘት ጮኽሁ፤ አንተም ድምፄን ሰማህ። ወደ ጥልቁ፣ ወደ ባሕሮች ልብ ጣልኸኝ፤ ሞገዶቹም ከበቡኝ፤ የሚንቀሳቀሱ ውሃዎችህና ማዕበሎችህ ሁሉ በላዬ ላይ ዐለፉ። ከዚያም፣ “ከፊትህ ተገፍቼ ተባረርሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና ወደ ቅዱሱ መቅደስህ እመለከታለሁ” አልሁ። ውሃዎቹ እስከ ሞት ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁም ዙሪያዬን አጠረኝ፤ ሐሩርም በራሴ ላይ ተጠመጠመ። እስከ ተራሮች መሠረት ድረስ ሰጠምሁ፤ ምድርም በሮቿን በኋላዬ ለዘላለም ዘጋች። አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣሃት፣ አባቴ። ሕይወቴ እያለቀች ስትሄድ አባቴን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱሱ መቅደስህ ወጣ። ከንቱ ጣዖታትን አጥብቀው የሚይዙ ሊኖራቸው የሚችለውን ፍቅር ትተው ይሄዳሉ። እኔ ግን በምስጋና ድምፅ መሥዋዕትን አቀርብልሃለሁ፤ የተሳልሁትን ስእለት ሁሉ እፈጽማለሁ። ድነት የአባታችን ነው!

ከዚያም አባታችን ዓሣውን ተናገረው፤ ዓሣውም ዮናስን ወደ የብስ ላይ ተፋው።